RESOURCES (Amharic) | rpru
top of page

ጥያቄ ካለዎት ከታች ያሉትን ምልክቶች በመጠቀም ይደውሉ ወይም ኢሜይል ይላኩልን።

መረጃ ማግኛ ዘዴዎች

በይፋዊነት እና በግል ድጋፍ የተደረገባቸው በዓለም ዙሪያ ሰው የተሳተፈባቸው የክሊኒክ ጥናቶችን የያዘ የመረጃ ክምችት።

ይህ ጣቢያ የግል ታሪኮችን፣ የምርምር ጥናቶች እንዴት ማግኘት እንደሚቻል እና በተጨማሪም የምርምር ጥናትን የሚመለከቱ ቃሎችና ሀረጎች ትርጉም ይገኛል።

NeedyMeds የጤና እንክብካቤ ወጫቸውን መሸፈን ያልቻሉ ሰዎችን ለመደገፍ የተዘጋጁ ፕሮግራሞችን የሚመለከት መረጃ የሚያቀርብ የኢንተርኔት ላይ የመረጃ ምንጭ ነው። ሁሉም መረጃ ነጻ፣ ለማግኘት ቀላል እና በየጊዜ የሚሻሻል ነው። ምንም ምዝገባ ማድረግ አያስፈልግም እንዲሁም ምንም አይነት የግል መረጃ አይጠይቁም።

ይህ ጣቢያ፣ በሂዩማን ሪሰርች ፕሮቴክሽን (OHRP) የተዘጋጀ ሲሆን፣ በጎ ፈቃደኛ የሚሆኑ የምርምር ጥናት ተሳታፊዎች በመረጃ ላይ በመመስረት እንዲወስኑ ስለ ምርምር ጥናት መሰረታዊ መረጃ ለማህበረሰቡ ያቀርባ።

CenterWatch ለለታማሚዎች ስለ የምርምር ጥናት አስፈላጊ የጤና እና የትምህርት መረጃዎችን በማቅረብ ስለ የክሊኒክ ምርምሮች እና ተሳትፎ ያሳውቃል እንዲሁም ሌሎች ስለ ህክምና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጡ ድርጅቶችን በተመለከተ ያሳውቃል።

የተለጠጠ ተደራሽነት ማለት በጥናት ላይ ያለን የህክምና መገልገያ (ለምሳሌ በFDA ማረጋገጫ ያልተሰጠው) ከክሊኒካል ሙከራ ውጪ ለሆነ ተግባር መጠቀም ማለት ነው። እዚህ ተጨማሪ መረጃ ያገኛሉ

ፔሸንት አድቮኬት ፋውንዴሽን የህክምና እርዳታ ከማግኘት፣ የህክምና እዳ፣ እና ከመታመም ጋር በተያያዘ የስራ ቅጥርን ማቆየትን በሚመለከት የክርክር፣ የድርድር እና ሽምግልና ስራዎችን ለበሽተኞች ያቀርባል።

•    ፔሸንት ትራቭል
ፔሸንት ትራቭል ሪፈራል ፕሮግራም ሁሉንም አይነት በበጎ አድራጎት የሚቀርቡ ከህክምና ጋር ተያያዥ የሆኑ የረጅም-እርቀት የጉዞ አገልግሎቶችን በሚመለከት መረጃ እንዲሁም ለሁሉም በብሄራዊ የበጎ አድራጎት የህክምና አገልግሎት ትሥሥር የሚቀርቡ መረጃዎችን ያቀርባል። 

የምርምር ጥናት ይፈልጉ

ከዚህ በታች ከGHUCCTS ተቋማት ውስጥ በአንደኛው የበጎ ፈቃደኛ ተሳታፊዎችን የሚቀበሉ ጥናቶችን ዝርዝር ያገኛሉ፦ ጆርጅያታውን ዩኒቨርሲቲ፣ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ሜድስታር የጤና ምርምር ኢንስቲቲዩት፣ ወይም ዋሽንግተን ዲሲ ቪኤ ሜዲካል ሴንተር። ለእርስዎ የሚሆን ጥናት ለማግኘት እንዲያግዘን እባክዎ የፍለጋ መስፈርትዎን ከታች ያስገቡ። ፍለጋውን ማድረግ የሚችሉት በእንግሊዝኛ ብቻ ነው። ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ ኢሜይል ይላኩልን ወይም 301-560-2963 ላይ ይደውሉ።

bottom of page