ስለ ተሳታፊ አባልት (GHUCCTS)
የጆርጅታውን-ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲዎች ክሊኒካል እና ትራንስሌሽናል ሳይንስ ማዕከል (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል GHUCCTS በሚል ይጠቀሳል)፣ የክሊኒክ ምርምሮችን እና የትራንስሌሽን ሳይንስ ለማበረታታት ከሚመነጭ ፍላጎት የተመሰረተ የህክምና ምርምሮችን የሚያካሂዱ የብዙ-ተቋማት መድረክ ነው። የGHUCCTS መድረክ አባላት፦ ጆርጅያታውን ዩኒቨርሲቲ (GU)፣ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ (HU)፣ MedStar የጤና ምርምር ተቋም (MHRI)፣ ኦክ ሪጅ ብሄራዊ ላቦራቶሪ (ORNL)፣ እና ዋሽንግተን ቬተራንስ አፌርስ ሜዲካል ሴንተር (VAMC)።
በአባል ተቋማት መካከል ባለ አጋርነት እና ትብብሮች፣ GHUCCTS በጤና እንክብካቤ መስክ ሳይንሳዊ መሻሻሎችን ለማምጣት ክሊኒካል ምርምርን እና ትራንስሌሽናል ሳይንስን እየቀየረው ነው።
GHUCCTS የተመሰረተው በሁሉም አባል ተቋማት ተቀባይነት ባገኙ በስድስት መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳቦች ላይ ነው። እነዚህም የመድረኩን አጠቃላይ ዓላማ እንዲሁም ቁልፍ የምርምሩን እንቅስቃሴዎች ባህሪያት፣ አገዛዝ እና ትኩረት ለመለየት ያገለግላሉ። እነዚህ ጽንሰ ሃሳቦች የእራሱ የመድረኩን መሰረቶች፣ እንዲሁም የGHUCCTS የምርምር እና የትምህርት ፕሮግራሞች ይፈጥራሉ። (georgetownhowardctsa.org)
ስለ GHUCCTS ተጨማሪ ለማወቅ፦
GHUCCTS ይጎብኙ